የእርስዎ ጥያቄዎች ተመልሰዋል።

1. ኤምካስ (MCAS) ምንድን ነው?

ኤምካስ ወይም በዘዴ የመንቀሳቀስን ችሎታ የሚያሳደግ (MCAS - Maneuvering Characteristics Augmentation System) በ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX ) ላይ ተግባራዊ የተደረገ የበረራ መቆጣጠሪያ ሕግ ሲሆን ዓላማውም የአውሮፕላን አያያዝ ባህርያትን ለማሻሻልና ከፍ ባለ ቅስት ወይም የዕይታ ዘዌ (አንግል ኦፍ አታክ) ጊዜ የማሸቀብ ዝንባሌን ለመቀነስ ነው።

2. ቦይንግ ኤምካስን (MCAS) በ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) ላይ የጫነው ለምንድን ነው?

በዘዴ የመንቀሳቀስን ችሎታ የሚያሳደግ (Maneuvering Characteristics Augmentation System (MCAS) የበረራ መቆጣጠሪያ ሕግ ለ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) የተዘጋጀና የዕውቅና ማረጋገጫ ያገኘ ሲሆን አውሮፕላኑ እንደ ሌሎች ፯፻፴፯ (737) አውሮፕላኖች ሆኖ እንዲበር ለማስቻል የአውሮፕላኑን የሽቅብ በረራውን የመረጋጋት ሁኔታ ያጎለብታል።

3. ኤምካስ (MCAS) የሚነቃው ወይም የሚተገብረው መቼ ነው?

ኤምካስ (MCAS) መተግበር የሚጀምረው አልፎ አልፎ ሲሆን የሚከተሉት ሶስት ሁኔታዎች ሲከሰቱ ነው፡
  • የአውሮፕላኑ አፍንጫ ከተለመደው የበለጠ ዘዌ (ማዕዘን) ሲጠጋ።
  • አብራሪው በእጅ ጉልበት ሽቅብ ሲበር።
  • የአውሮፕላኑ ክፈፎች ወደ ላይ ሲሆኑ።

4. የዕይታ ዘዌ ወይም ማዕዘን (አንግል ኦፍ አታክ) ምንድን ነው?

የዕይታ ዘዌ ማለት በሽቅብ ዘዌ (የአውሮፕላኑ የአፍንጫ አቅጣጫ) እና ወደርሱ በሚመጣው ነፋስ ዘዌ መካከል ያለው ልዩነት ነው።

5. በዚህ የሶፍትዌር ማሻሻያ የኤምካስ ለውጥ ምንድነው?

ቦይንግ የኤምካስ (MCAS) ሶፍትዌር ማሻሻያን ያዘጋጀው የዕይታ ዘዌን (አንግል ኦፍ አታክ) አነፍናፊ ዳሳሾች (ሴንሰሮች) የተሳሳተ መረጃ ቢያስተላልፉ ተጨማሪ የጥበቃ ሽፋን ለመስጠት ነው። ተጨማሪ የጥበቃ ሽፋኖች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡
  • የበረራ መቆጣጠሪያ ስርዓቱ ከሁለቱም የዕይታ ዘዌ (አንግል ኦፍ አታክ) አነፍናፊ ዳሳሾች (ሴንሰሮች) የሚመጡትን ግባቶችን ያነጻጽራል። ክፈፎቹ በተሰበሰቡበት ጊዜ አነፍናፊ ድሣሾቹ (ሴንሰሮቹ) በ፭.፭ (በአምስት ነጥብ አምስት ዲግሪ) ወይም በላይ ልዩነት ካልተስማሙ ኤምካስ (MCAS) አይነቃም ወይም ስራ አይጀምርም። በበረራ መቆጣጠሪያ ዓምድ ላይ ለአብራሪዎቹ በመረጃ ማስጠንቀቂያ መብራት ይጠቆማሉ።
  • MCAS መደበኛ ባልሆኑ ሁኔታዎች ከነቃ ወይም ከሰራ፣ ለእያንዳንዱ ከፍያለ የዕይታ ዘዌ (አንግል ኦፍ አታክ (AOA) ክስተት አንድ ግቤት ብቻ ያቀርባል። ኤምካስ (MCAS) ተስኖት ከአንድ በላይ ግቤቶችን ይሰጣል ተብሎ የሚታወቁ ወይም የሚገመቱ ሁኔታዎች የሉም።
  • ኤምካስ (MCAS) የበረራ ሰራተኞች የበረራ ዓምዱን በመሳብ ሊቋቋሙት ከሚችሉት በላይ በተጨማሪ የማረጋጊያ ግቤት በጭራሽ ማዘዝ አይችልም። አብራሪዎቹ (ፓይለቶቹ) ሁልጊዜ ኤምካስን (MCAS) ወደ ጎን በማለት አውሮፕላኑን በእጅ ጉልበት የመቆጣጠር ችሎታ ይኖራቸዋል።
  እነዚህ ማሻሻያዎች የበረራ ሰራተኞች መደበኛ ባልሆኑ የበረራ ሁኔታዎች ጊዜ የሚፈጠርባቸውን የስራ ጫና የሚቀንሱ ሲሆን፣ ኤምካስ (MCAS) በተሳሳተ መረጃ ስራ እንዳይጀምር ይከላከላል።

6. ቦይንግ ለደህንነት ባህርያት ማሳያ ክፍያ ያስከፍላል?

፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) አውሮፕላንን ደህንነቱ በተጠበቀና ብቃት ባለው መንገድ ለማንቀሳቀስ የሚያስፈለጉ ተቀዳሚ የበረራ መረጃዎቸ በሙሉ በመሰረታዊው የቀዳሚ በረራ ማሳያ ውስጥ ተካትተዋል። ይህ በሁሉም የመንገደኞች ማመላለሻ ምርቶቻችን ላይ እውን የሆነ ነው። ቦይንግ አስፈላጊ በሆኑ የደህንነት ባህርያት መስፈርት ላይ የገንዘብ ዋጋ አያስቀምጥም።   የአውሮፕላን ሰራተኞች የሚከተሉት አሰራርና አውሮፕላኑ ደህንነቱና ብቃቱ በተጠበቀ መንገድ እንዲንቀሳቀስ ማስቻል ትኩረት የሚያደርጉት በአውሮፕላን የመጠቅለል እና የሽቅብ ባህርይ፣ ከባህር ወለል ከፍታ፣ የወደፊትና የተዳፋት ፍጥነት ላይ ሲሆን እነዚህ ሁሉ ደግሞ በተቀዳሚ የበረራ ማሳያ ገጽ ውስጥ የሚካተቱ ናቸው። ሁሉም የ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) አውሮፕላኖች ይህን መረጃ የሚያሳዩበት መንገድ ከፓይለት ስልጠና እና ፓይለቶች እንዲጠቀሙበት ከሰለጠኑበት ከመሰረታዊ መሳሪያ መቃኛ ሃረግ ጋር ወጥነት ባለው መልኩ ነው። አንዳንድ ደንበኞች የራሳቸው የሆነ ተያያዥነት ያለው የስልጠና መስፈርቶች ያላቸው ሲሆን በተቀዳሚ መረጃ ማሳያ ገጽ ላይ የዕይታ ዘዌ (አንግል ኦፍ አታክ) መረጃን እንድንሰጣቸው ጠይቀውናል፤ እኛም ያንን መረጃ ለመስጠት አቅም ማሳደጊያ አማራጩን አቅርበንላቸዋል። ይሁን እንጂ፣ ይህን ልዩ ባህርይ በተቀዳሚ የበረራ ማሳያቸው ውስጥ ማካተት የሚፈልጉት ደንበኞች ሁሉም አየደሉም፣ ስለዚህ እንደ በደንበኛ ምርጫ ተደርጎ ይቀርባል። በሶፍትዌሩ ማሻሻል ምክንያት ደንበኞች ለዕይታ ዘዌ (አንግል ኦፍ አታክ) ልዩነት ማሳያ ባህርይ ወይም የዕይታ ዘዌ ጠቋሚ አማራጭን በመምረጣቸው ክፍያ አይጠየቁም።

7. ለደንበኞች ስንት ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) አውሮፕላኖች አስረክበናል?

እስከ ጥር ፳፻፲፩ (ሁለት ሺህ አስራ አንድ) ወይም እ.አ .አ ፌብርዋሪ ፳፻፲፱ (ሁለት ሺህ አስራ ዘጠኝ) ቦይንግ ፫፻፸ (ሶስት መቶ ሰባ) ማክስ (MAX) አዎሮፕላኖችን ለ፵፯ (አርባ ሰባት) ደንበኞች አስረክቧል።

8. ተጨማሪ ስንት ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) አውሮፕላኖች ታዘዋል ?

፻፯ (አንድ መቶ ሰባት) ደንበኞች ወደ ፶፻ (አምስት ሺህ) ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) አውሮፕላኖች እንዲመረቱላቸው ትእዛዝ ሰጥተዋል።

9. ቦይንግ ፯፻፴፯ ማክስን (737 MAX) ለማምረት የወሰነው እንዴትና ለምንድን ነው?

የግንባታ ጥረቶቻችን ሁልጊዜ የሚጀምሩት የደንበኞቻችንን ፍላጎትና መስፈርቶቻቸውን ለመረዳት እነሱን በማዳመጥ ነው። በደንበኞች ግብረ-መልስ እና ከገበያ በተገኘ መረጃ መሰረት፣ ኔክስት ጀነሬሽን ፯፻፴፯ን (Next-Generation 737) ለመተካት በግልጽ የተገኘው ምርጫ ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) ነበር። ለስድስት ዓመታት ያህል ቡድናችን በስነ ስርዓት የታነጸ ስልታዊ ምርት የማውጣት ሒደትን በማለፍ የአውሮፕላኑን ደህንነትና ብቃት ትክከለኛነት ያረጋገጠ ጠንካራ የሙከራ መርሃ ግብር አዘጋጀ።

ተጨማሪ የ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) የመረጃ ምንጮች

የአየር በረራን ለሁሉም ለማሻሻል ፣ ከአምራቾች፣ ከቁጥጥር ባለስልጣኖች፣ ከአብራሪዎችና፣ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አየር መንገዶች ጋር አብረን ለመስራት እያደረግናቸው ስላሉ ጥረቶች ተጨማሪ መረጃ እነሆ።

የመረጃ ምንጮች