የ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) አዳዲስ መረጃዎች

ወቅታዊ ዜና፣መግለጫዎች እና መረጃዎች

ቦይንግ ባለፉት በርካታ ወራት ውስጥ ፯፻፴፯ ማክስን (737 MAX) ደህንነቱ በተጠበቀ መንገድ ወደ አገልግሎት ይመለስ ዘንድ ከፍተኛ ማሻሻያዎችን ያደረገ ሲሆን ኩባንያው የ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) ሶፍትዌር እና ተዛማጅ የስልጠና ብቃትን ለማረጋገጥ የተቀመጠውን ሒደት በተመለከተ ከኤፍኤኤ (ፌደራል አቪዬሽን አድምንስትሬሽን (FAA)) እና ከሌሎች አለም አቀፍ የቁጥጥር ባለስልጣኖች ጋር በትብብር መስራቱን እንደቀጠለ ነው። ኩባንያው የበለጠ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ የሆኑ አስተዳደራዊና የክወና ለውጦችን አድርጓል። እነዚህ ሁለት አሳዛኝ አደጋዎች በእያንዳንዱ የቦይንግ ሰራተኛ ላይ ከባድ ተጽእኖ ማሳደሩን ይቀጥላል። በእነዚህ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦችና የማህበረሰቦችን ፍላጎት ለማሟላት የአንድ መቶ ሚሊዮን (፼፼) የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ማድረጊያ ገቢ መድበናል።

ደህንነት። ጥራት። ሐቀኝነት።

በመላው የአየር ማመላለሻ ስርአተ ምህዳር ውስጥ ደህንነትን በቀጣይነት ለማዳበር ቁርጠኞች ነን።

የእርስዎ ጥያቄዎች። ተመልሰዋል።

በ፯፻፴፯ ማክስ(737 MAX) ላይ ስላለዎት ጥያቄ እና ፯፻፴፯ ማክስን (737 MAX) ደህንነታቸው ከተረጋገጠላቸውና አስተማማኝ ሆነው ከሚበሩ አውሮፕላኖች ውስጥ አንዱ እንዴት እንደምናደርገው በተመለከተ ላለዎት ጥያቄዎች ምላሽ ያግኙ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ያግኙ

የሰራተኞች ድምፅ

የ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) አሳዛኝ አደጋዎች በሰራተኞቻችን ላይ ጥልቅና ግላዊ የሆነ ተጽዕኖ አሳድሯል። ሰራተኞቻችን ፤ ፯፻፴፯ ማክስን (737 MAX) ደህንነታቸው ከተረጋገጠላቸው መቼውንም ጊዜ ከሚበሩ አውሮፕላኖች ውስጥ አንዱ ለማድረግ ያላቸው ቁርጠኝነተና የነሱ ምላሽ ምን እንደሆነ ያድምጡ።

ተጨማሪ የ፯፻፴፯ ማክስ (737 MAX) መረጃዎች

የበረራን አገልግሎት ለሁሉም ለማሻሻል ከአምራቾች፣ ከቁጥጥር ባለስልጣኖች፣ ከአብራሪዎችና በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አየር መንገዶች ጋር አብረን ለመስራት እያደረግናቸው ስላሉ ጥረቶች ተጨማሪ መረጃ እነሆ።

የመረጃ ምንጮች